የቪዥንፈንድ ማይክሮፋይናንስ ተቋም አመታዊ የማኔጅመንት ጉባኤ ሀምሌ 10 እና 11 2017 ዓ.ም. በኃይሌ ግራንድ ሆቴል ተካሂዷል፡፡
በጉባዔው ላይ የተቋሙ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ታዬ ጭምዴሳን ጨምሮ የዋናው ቢሮ የተለያዩ የስራ ክፍል ሃላፊዎች፤ የአካባቢ ስራ አስኪያጆች እንዲሁም የ116ቱም ቅርንጫፎች ስራ አስኪያጆች ተገኝተዋል፡፡


በዕለቱ የ2024/25 (እ.ኤ.አ) የበጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ለጉባዔው ከቀረበ በኋላ ሰፊ ውይይት የተደረገበት ሲሆን የዕርስ በዕርስ የልምድ ልውውጥ በማድረግ ውጤታማ ተሞክሮዎችን ለመተግበር የሚያስችል የፓናል ዉይይትም ተደርጓል። በተጨማሪም ተቋሙ በቀጣይ አመት ለመተግበር ያቀዳቸውን አዳዲስ አቅጣጫዎች የሚያመላክቱ ገለጻዎች ቀርበዋል፡፡

ከውይይት በኋላ የማጠቃለያ ሃሳብ ያስተላለፉት አቶ ታዬ ጭምዴሳ ሁሉም ተሳታፊ አካላት የቁጠባ መጠን ማሳደግን፤ የተቋሙን ወጪ እና የሚበላሹ ብድሮችን መጠን መቀነስን እንዲሁም የላቀ የደንበኞች አገልግሎ ት አሰጣጥን በተመለከተ ልዩ ትኩረት በመስጠት መስራት እንደሚጠበቅ አሳስበዋል፡፡

በመጨረሻም የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ሰራተኞች የዕውቅና መስጠት መርሃግብር የተከናወነ ሲሆን ሽልማቱን የሰጡት የተቋሙ የቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ እሌኒ መርጊያ ባስተላለፉት መልዕክት ከመደበኛው ስብሰባ ባሻገር፣ ይህ መድረክ የእርስ በእርስ ትስስር እንዲፈጠር እና ወዳጅነት እንዲጠናከር በማድረግ በኩል ያለው ፋይዳ ትልቅ መሆኑን ገልፀው ሁሉም ሰው ተቋሙ የደረሰበትን የእድገት ደረጃ ባገናዘበ መልኩ በባለቤትነት ስሜት በመስራት ከዚህ በእጅጉ የሚልቅ ውጤት ለማስመዝገብ ተግተው እንዲሰሩ ከአደራ ጭምር አሳስበዋል፡፡




