Locate our branches

Contact Us
Contact Us

ቪዥንፈንድ ማይክሮፋይናንስ ከቪዥን ኮሚኒቲ ሆልሰቲክ ጋር በመሆን የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሄደ።

ቪዥንፈንድ ማይክሮፋይናንስ ከቪዥን ኮሚኒቲ ሆልሰቲክጋር በመተባበር “አረንጓዴ ለአካባቢያችን፤ አካታች ፋይናንስ ለህዝባችን” በሚል መሪ ሀሳብ የችግኝ ተከላመርሃ ግብር አካሄደ።

በመርሃ-ግብሩ ላይ የተቋሞቹ ከፍተኛ የሥራ አመራሮች፣ሠራተኞች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። በዕለቱም በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 (ፈረንሳይ ግሬት አቢሲኒያ አካባቢ)እና በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 (ገነተ ፍሬ ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ) ችግኞች ተተክለዋል።

የተቋሙ አመራሮች እና ሠራተኞች እንደገለጹት፣የተተከሉት ችግኞች ለቀጣዩ ትውልድ ንጹህ አየር፣ ጤናማ አካባቢ እና ዘላቂ ልማት የሚያስገኙ ሕያው አሻራዎች ናቸው ብለዋል። ተቋሙ የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ ጎን ለጎን፣ መሰል ማህበራዊና አከባቢያዊ ኃላፊነቶችን በንቃት መወጣቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተገልጿል።




© Copyright Vision Fund MFI . All rights reserved.

Developed By

Developed By