ያግኙን

ቪዥንፈንድ ማይክሮፋይናንስ የአገልግሎት አሰጣጡን በዲጂታል ፋይናንስ ዘርፍ ይበልጥ ለማዘመን የሚያስችለውን የጋራ ስምምነት ከሳንቲም ፔይ ጋር ተፈራርሟል።

ይህ ስምምነት ተቋሙ ላለፉት 27 ዓመታት በመደበኛ የፋይናንስ አገልግሎት ያስመዘገበውን ስኬት ወደ ዲጂታል ምህዳር ለማሸጋገር ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በተጨማሪም ስምምነቱ ለደንበኞች እና ለነጋዴዎች አስተማማኝ፣ ምቹ እና ደህንነቱ የተጠበቀ የክፍያ አማራጮችን በማቅረብ የሁለቱን ተቋማት የጋራ ስኬት እንደሚያረጋግጥ ተመልክቷል።

በመጨረሻም ይህ አጋርነት የሁለቱንም ተቋማት ተወዳዳሪነት የሚያሳድግ ሲሆን፣ በቀጣይም ደንበኞችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ አዳዲስ የፋይናንስ አገልግሎቶችን በጋራ ለማቅረብ መሰረት የሚጥል መሆኑ ተገልጿል።

© የቅጂ መብት ቪዥን ፈንድ MFI . ሁሉም መብቶች የተጠበቁ ናቸው።

የተገነባው በ

የተገነባው በ