ያግኙን

ቪዥንፈንድ ማይክሮፋይናንስ አዳዲስ ቅርንጫፎችን መርቆ ከፈተ።

ተቋሙ በደማቅ የመክፈቻ ስነ-ስርዓት የቱሉዲምቱ እና ሳሪስ ቅርንጫፎችን በይፋ ስራ አስጀምሯል። በመክፈቻው ሥነ–ሥርዓት ወቅት የዋናው ቢሮ ተወካዮች፥ የማስተባበሪያ ፅ/ቤት ሃላፊዎች፣ የአከባቢው ማህበረሰብ ተወካዮች እና የተለያዩ ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።

አዳዲሶቹ ቅርንጫፎች ለማህበረሰቡ በቅርበት ተደራሽ በመሆን ምቹና ቀልጣፋ አገልግሎት በማቅረብ በኩል የሚኖራቸው ፋይዳ ጉልህ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በዕለቱ የተገኙ ታዳሚዎችም አማራጭ የፋይናንስ አቅርቦት የሚሰጡ ቅርንጫፎች በአካባቢያቸው መከፈታቸው እንዳስደሰታቸውና በቀጣይም አብረው ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል።

በመጨረሻም ተቋሙ በቀጣይም ተደራሽነቱን በማስፋት ለማህበረሰቡ የተሻለ አገልግሎት ለማቅረብ በቁርጠኝነት የሚሰራ መሆኑ ተመልክቷል።

© የቅጂ መብት ቪዥን ፈንድ MFI . ሁሉም መብቶች የተጠበቁ ናቸው።

የተገነባው በ

የተገነባው በ