ያግኙን

ቪዥንፈንድ ማይክሮፋይናንስ ተቋም አ.ማ. ከሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ፡፡

ታህሳስ 13፥2018 ዓ.ም. በስካይላይት ሆቴል በተካሄደው የፊርማ ስነ ሥርዓት ላይ እንደተገለፀው በስምምነቱ መሰረት ተቋሙ ቀልጣፋና ዘመናዊ የሆነ የውክልና፣የመመስረቻና ተያያዥ ሰነዶችን በአጭር ጊዜና በዲጂታል መንገድ ለማረጋገጥ የሚያስችለው ይሆናል። በተጨማሪም የስጋት አስተዳደር ስርዓትን በመዘርጋት የደንበኞችን የዋስትና ሰነዶች ደህንነት በመጠበቅና የሰነዶችን ህጋዊነት በማረጋገጥ የተቋሙን አሰራር ውጤታማነት እንደሚያጎለብት ተገልጿል።

በመጨረሻም ስምምነቱ ደንበኞቻችን ሰነዶችን ለማረጋገጥ የሚወስድባቸውን አላስፈላጊ ጊዜና ወጪ በእጅጉ በመቀነስ የደንበኞችን እርካታ ለማረጋገጥ የሚያስችል መሆኑ ተመልክቷል።

© የቅጂ መብት ቪዥን ፈንድ MFI . ሁሉም መብቶች የተጠበቁ ናቸው።

የተገነባው በ

የተገነባው በ